የአንተ ወዳጅ

Jesus is your friend

ኢየሱስ የአንተ ወዳጅ

እኔ አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ እርሱ ከወዳጆቼ ሁሉ ይልቅ የቅርብ ወዳጄ ነው፡፡ እርሱ በጣም ደግና እውነተኛ ስለሆነ አንተም እንድትተዋወቀው እፈልጋለሁ፡፡ ስሙ ኢየሱስ ይባላል፡፡ እርሱ የአንተም ወዳጅ መሆን ስለሚፈልግ በጣም ድንቅ ነገር ነው፡፡

ስለ እርሱ ልንገርህ፡፡ የእርሱን ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትና የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡

የተሟላ መልዕክት ክፍል የአንተ ወዳጅ

አለምና በአለም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ የሰማይና የምድር አምላክ ነው፡፡ እርሱ ሕይወትንና እስትንፋስን ለሁሉም ይሰጣል፡፡

God's creation

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ ኢየሱስ የግል አዳኛችን እንዲሆን እግዚአብሔር ከሰማይ ላከው፡፡ እግዚአብሔር ዓለሙን በጣም ስለወደደ (ያ ማለት አንተንና እኔን ወደደ ማለት ነው) አንድያ ልጁ የሆነው ኢየሱስን ለኃጢአታችን እንዲሞትና የሚያምንበት ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ወደ አለም ላከው (ዮሐንስ 3፥16)፡፡

ኢየሱስ ወደ ምድር እንደ ትንሽ ሕጻን ልጅ መጣ፡፡ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት አባትና እናቱ ዮሴፍና ማርያም ነበሩ፡፡ እርሱ በጋጣ ተወልዶና በግርግም ተኝቶ ነበር፡፡

Jesus' birth

ኢየሱስ ከዮሴፍና ማርያም ጋር አድጓልና ታዘዛቸው፡፡ አብሯቸው የሚጫወታቸው ወንድሞችና እህቶች ነበሩት፡፡ ዮሴፍንም በአናጺነት ስራው ያግዘው ነበር፡፡

Jesus and the lad with food

ኢየሱስ ትልቅ ሰው ሲሆን ሰዎችን ስለ ሰማይ አባቱ አስተማራቸው፡፡ እግዚአብሔር እንደሚወዳቸው አሳያቸው፡፡ ሕመምተኞችን ፈወሰ፤ በችግር ወስጥ የነበሩትንም ሁሉ አጽናና፡፡ ኢየሱስ የልጆች ወዳጅ ነበር፡፡ ልጆች ወደ እርሱ እንዲቀርቡ ፈለገ፡፡ ለእንርሱም ጊዜ ሰጣቸው፡፡ ልጆች ኢየሱስን ወደዱት፤ ከእርሱም ጋር አብረው ጊዜ ማሳለፍን ይወዱ ነበር፡፡ 
አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን አልወደዱትም፡፡ ተመቀኙትና ጠሉት፡፡ በጣም ስለጠሉትም ሊገድሉት ፈለጉ፡፡ አንድ አሰቃቂ ቀን ኢየሱስን በመስቀል ሰቅለው ገደሉት፡፡ ኢየሱስ ምንም በደል አልሰራም ነበር፡፡ አንተና እኔ ስለ በደልን እርሱ በቦታችን ሞተ፡፡

Jesus on the cross

የኢየሱስ ታሪክ በሞቱ አያበቃም፡፡ እግዚአብሔር ከሞት አስነሳው! ተከታዮቹም አዩት፡፡ ከዛም አንድ ቀን ወደ ሰማይ ተመለሰ፡፡
ዛሬ እርሱ ሊያይህና ሊሰማህ ይችላል፡፡ እርሱ ስላንተ ሁሉን ያውቃል፤ ይጠብቅህማል፡፡ በጸሎት ወደ እርሱ ና፡፡

Jesus listening to a woman pray

 

 

ለተጨማሪ መረጃ ያግኙን

በረሪ የውንጌል ጽሑፎችን (ትራክቶችን) ለማዘዝ