ከሞት በኋላስ?

በአሁኑ ወቅት ሕያው ነዎት፤ ይተነፍሳሉ፤ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ፤ ስራዎንም ያከናውናሉ፡፡ እየኖሩ ያሉት ሕይወት በምቾት ወይም በችግር የተሞላ ሕይወት ይሆናል፡፡ ፀሀይ ትወጣለች ደግሞም ትጠልቃለች፤ በአንድ ስፍራ ህጻን ይወለዳል በሌላ ስፍራ ደግሞ አንዱ ይሞታል፡፡

ሕይወት በአጠቃላይ ጊዜያዊ ቅንብር ነች፡፡

ነገር ግን

እርስዎ ከሞቱ በኋላ ወዴት ይሄዳሉ?

ኃይማኖተኛ ሰው ቢሆኑ፤ ወይም

ምንም አይነት ኃይማኖት ባይኖርዎ

ይህንን መሰረታዊ ጥያቄ መመለስ

ይኖርብዎታል፡፡ ምክንያቱም ሰው

ሁሉ ከአጭር የምድራዊ ቆይታው

በኋላ ወደ ዘላለም መኖሪያው

ያመራልና (መክብብ 12፡5)፡፡

ግን ወዴት?

የሚቀበሩበት የመቃብር ስፍራ ነፍሶን ማስቀረት አይቻለውም፡፡ በድንዎ በእሳት ተቃጥሎ ቢጠፋ፤ ነፍስዎን እሳት አይበላትም፡፡ በጥልቁ ባህር ውስት ገብተው ቢጠፉ፤ ነፍስዎ አትሰምጥም፡፡

ነፍስዎ በፍጹም አትሞትም!

የሰማይ እና የምድር ሁሉ አምላክ

የተሟላ መልዕክት ክፍል ከሞት በኋላስ?

“ነፍስ ሁሉ የኔ ናት” ብሎአል፡፡

ከዚህ ሕይወት በኋላ እውነተኛ ማንነትዎ የሆነችው ነፍስዎ፤ በሕይወት በምድር ላይ በነበሩበት ወቅት ከሰሯቸው መልካምም ይሁን ክፉ ስራዎት ጋር ትገናኛለች፡፡ ዕብራውያን 9፡27ን መልከቱ፡፡

ከልብዎ የሚያመልኩ ሰው ይሆኑ ይሆናል

ስለሚሰርዋቸው ያለተገቡ ተግባራት ይጸጸቱ ይሆናል

የሰረቁትን መልሰው ይሆናል

እነዚህ ሁሉ የሚያስፈልጉ ነገሮች ቢሆኑም

ስለ ኃጢአትዎ በራስዎ ስርየትን ማምጣት አይችሉም

በምድር ሁሉ ላይ ፈራጅ የሆነው የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ከፊቱ የተሰወረ አንዳች ነገር ስለሌለ የእርስዎን ኃጢአት እና ሕይወት በአጠቃላይ ያውቃል፡፡ እርስዎ ከነኃጢአትዎ ከሆኑ ሊመጣ ካለው ከእግዚአብሔር ክብርና ባርኮት ሊካፈሉ አይችሉም፡፡

ነገር ግን የኸው የሰማይ አምላክ የፍቅር አምላክ ነው፡፡ ለሕወትዎና ለነብስዎ የመዳኛ መንገድ ስላዘጋጀ የዘላለም ጥፋት ወደ ሆነው ወደ ገሃነም እሳት መጣል የለብዎትም፡፡ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወደዚህ ምድር የላከው የእርስዎን ነብስ ለማዳን ነው፡፡ ኢየሱስ በቀላንዮ መስቀል ላይ ተሰቃይቶ ሲሞት የእርስዎ ኃጢአት ሁሉ በእርሱ ላይ ሆንዋል፡፡ እግዚአብሔር ሰማይ ሊያቀርብ የሚችለውን ድንቁን መስዋዕት ስለ እርስዎ ኃጢአት ሲል ሰጥትዋል፡፡ “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን” (ኢሳይያስ 53፥5)፡፡ እነዚህ የትንቢት ቃላት የተነገሩት ኢየሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ ከብዙ ዘመናት በፊት ነው፡፡

ኢየሱስ እንደሚወድዎ ያምናሉ? ወደ እርሱ በመጸለይ ኃጢአትዎን ይናዘዛሉ? ንስሀ በመግባት የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ያምናሉ? በፍጹም መሰጠት ወደ እርሱ ከመጡ ለነብስዎ ሰላምን እንዲሁም ከሞት በኋላ የከበረ ሕይወትን ይሰጥዎታል፡፡ በሀሴት የተሞላ የዘላለም ቤትና የነብስ ሰላም እንዳልዎት እርግጠኛ መሆን የሚችሉት ይህንን ወሳኔ ሲወስኑ ብቻ ነው፡፡

ግን’ኮ አዳኝ የሆነውን የኢየሱስን ፍቅር በሕይወት ዘመናቸው ላልተቀበሉ ሁሉ የጥፋት ጉድጓድና ማብቂያ የሌለው የዘልለም እሳት ይጠብቃቸዋል፡፡ ከሞት በኋላ ወደ ኋላ መመለስና የመዳን ተስፋ ሁሉ ያበቃለታል፡፡

“በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” (ማቴ. 25፥41)፡፡ “የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል” (ማቴ. 25፥30)፡፡  

እግዚአብሔር፤ በመጽሐፍ ቅዱስ፤ በምድር ሁሉ ላይ ሊመጣ ስላለው የመጨረሻ ፍርድ አስጠንቅቋል፡፡ በእነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ይህ የፍርድ ቀን ከመምጠቱ በፊት ግልጽና ተጨባጭ ምልክቶች እንደሚሆኑ ተጽፍዋል፡፡

ከመምጣቱ በፊት ጦርነትና የጦርነት ወሬ በየቦታው ይሰማል፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ ተነስቶ እርስ በእርስ አለመግባባት እና መፋጀት ይሆናል፤ መንግስታትም በመካከላቸው የሚነሳውን የሀሳብ ልዩነት እና አለመግባባት መፍታት ያቅታቸዋል፡፡

በተለያዩ ስፍራዎች የምድርም መናወጥና ቸነፈር ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ወቅት ክፉዎች በክፋታቸው እየባሱ እንደሚሄዱ ይነግረናል፡፡ ብዙዎችም የእግዚአብሔርን ማስጠንቀቂያ ቸል በማለት ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፡፡ በዘመናችን እነዚህን ትንቢቶቸ ሲፈጸሙ እያየን አይደለምን? ማቴዎስ 24፥6-7፤12 እና 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥4ን ይመልከቱ፡፡

አንድ ቀን ሁላችንም ለፈጸምናቸው ድርጊቶች ሁሉ ልንዳኝ ከፈጣሪያችን እና ጌታችን ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለን (ማቴዎስ 25፥32-33)፡፡ ጻድቅና ታላቅ ፈራጅ የሆነው አምላካችን በብልጽግናችን በድህነታችን፤ በእውቅናችን በመዋረዳች፤ በቆዳችን ቀለም፤ በዘራችን ላይ ያለተመሰረተ ጻድቅ ፍርድ እነደሚያስተላልፍ መዘንጋት የለብንም፡፡ 

ማብቂያ በሌለው ዘላለም ውስጥ የሰዓት መቁጠሪያና ዓመታዊ ቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) አይኖሩም፤ ዘመናቱም መጨረሻቸው አይታወቅም፡፡ የኃጢአተኞችና እግዚአብሔርን ያልፈሩቱ የስቃያቸው ጭስ ለዘላለም በገሀነም ሲጬስ፤ የዳኑቱ ደስታ ዝማሬ በረከትና መጽናናት ማብቂያ በሌለው በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ያስተጋባል፡፡ ምርጫዎን አሁኑኑ ይወስኑ፤ ምክንያቱም ይህ እድል በቅጽበት ከእጅዎ ሊወጣ ይችላልና፡፡ “እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው” (2ቆሮንጦስ 6፥2) ፤ ማቴዎስ 11፥28፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ያግኙን

በረሪ የውንጌል ጽሑፎችን (ትራክቶችን) ለማዘዝ